6 September 2020ታምሩ ጽጌ

ዓቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቶ ጨረሰ

ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በዋስ ከእሥር ተፈቱ

ከኦሮሚኛ ሙዚቃ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ ለየብቻቸው ታስረው የቆዩ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት እንዲቀላቀሉ ወይም እንዲገናኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው ነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ አቶ በቀለ ገርባ ቀደም ብሎ በነበረው ችሎት ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ነው፡፡

አቶ በቀለ በአቤቱታቸው ለፍርድ ቤቱ እንደገለጹት፣ እሳቸውና አቶ ጃዋር የታሰሩት ለየብቻቸው ነው፡፡ አየርም ሆነ የፀሐይ ብርሃን እያገኙ አይደለም፡፡ በመሆኑም አብረው እንዲሆኑ፣ አየርና የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኙ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ፣ እንዲቀላቀሉ ወይም እንዲገናኙ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

አቶ ሸምሰዲን ጠሀ የተባሉ ተጠርጣሪ (በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ የተካተቱ) ደግሞ በደረሰባቸው ድብደባ ጆሮአቸውን መታመማቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተው፣ በግልና በፈለጉት ሐኪም ቤት እንዲታከሙ ጠይቀው ፍርድ ቤቱ ቢፈቅድላቸውም አለመታከማቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

በችሎት የተገኙት የፌዴራል ፖሊስ ተወካይ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ እንዳስረዱት፣ ተጠርጣሪውን ጠይቀውት ‹‹እዚህ ሐኪም ቤት ውስዱኝ›› ስላላላቸው ፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሐኪም ቤት ወስደው እንዳሳከሙት ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ስለታመመና ሌላ ምርጫ ስላልነበራቸው መሆኑን አክለዋል፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪው ‹‹አልጠየቁኝም፣ ዝም ብለው ወስደውኝ ጠብታ ብቻ ነው የተሰጠኝ›› በማለቱ ዓቃቤ ሕግ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ዓቃቤ ሕግ በሰጠው አስተያየት፣ ተጠርጣሪውና ፖሊስ ሊተማመኑ ስላልቻሉ ተጠርጣሪ በችሎት የሚፈልገውን ሐኪም ቤት እንዲመርጥ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

ተጠርጣሪውም ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የሚገኘውን ዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል በመምረጥ እንዲታከም እንዲታዘዝለት በመናገሩ፣ ፍርድ ቤቱ በመረጠው ሐኪም ቤት እንዲታከም ፈቅዶለታል፡፡

በሌላ በኩል ዓቃቤ ሕግ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በከፈተው ቅድመ ምርመራ መዝገብ ላይ እንዲመሰክሩለት ከቆጠራቸው 15 ምስክሮች ውስጥ አሥሩን ካሰማ በኋላ ቀሪዎቹን እንደማይፈልጋቸው በመናገር፣ ምስክሮችን የመስማት ሒደቱ ነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ዓቃቤ ሕግም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 109 ድንጋጌ መሠረት ክስ የመመሥረቻ 15 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ግን የክስ መመሥረቻ ጊዜውን ተቃውመዋል፡፡ ዋስትናቸው እንዲከበርላቸውም ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል ከድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለ64 ቀናት በእስር ላይ የነበሩት ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በዋስ ተፈትተዋል፡፡ በታሰሩበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እሥረኛ ማቆያ (በትውስት) ሆነው፣ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በእስረኛ ማቆያ የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ተጠርጣሪዎች በመገኘታቸው ሥጋታቸውን ሲገልጹ የቆዩት የኢትዮጵያ ኃይሎች ንቅናቄ (ኢኃን) ሊቀመንበር ይልቃል (ኢንጂነር) ከተለመደው ወጣ ባለ ሁኔታ የራስ ፀጉራቸውና ፂማቸው ከማደጉ በስተቀር በሰላም መፈታታቸው ታውቋል፡፡

By Oromedia

Oromedia is a non profit organisation established to provide news, views, information, to provide training, to create awareness to the Oromo community in Victoria focusing on a range of current and relevant issues of Oromo national interest. It provides news and views on topics ranging from arts, culture, history, politics, education, healthcare, business,, sports, technology and science. Oromedia is the strategic use of media to promote public debate, and generate community support for changes in community norms and policies. Working for the goals of safe, healthy and prosperous communities, identifying barriers to strategic policy implementation, and sharing current research through media that improve the world we live in. The purpose of Oromedia is to provide information, to connect people, to promote knowledge and advancement through collection, production and dissemination of information, providing training, organising information session forums with the aim of sharing information, education and experiences among nation.

One thought on “አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ እንዲገናኙ ትዕዛዝ ተሰጠ”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *